እስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ እንደገና ጥቃትን ለመጀመር እየተዘጋጁ ነው
እስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ እንደገና ጥቃትን ለመጀመር ከፍተኛ ዝግጅቶችን እያካሄዱ እንደሆነ ኒውዮርክ ታይምስ ዘገበ። አዲሱ ጥቃት ከዚህ በፊት ከተፈፀሙት ሁሉ የጠነከረ ሊሆን እንደሚችል ሁለት ባለስልጣኖችን በመጥቀስ ጋዜጣው ዘግቧል።ጋዜጣው የጠቀሳቸው የአሜሪካ ኃላፊዎች እንደሚሉት፣ በኢራን ላይ እንደገና ሊደረጉ ከታሰቡት የተቀናጁ ጥቃቶች መካከል ከባድ የቦምብ ጥቃቶችን በወታደራዊና መሠረተ ልማት ኢላማዎች ማካሄድ፣ በሰሜናዊ ባሕረ ሰላጤ በኻርግ ደሴት የሚገኘውን እና ኢራን ነዳጅ ለውጭ ገበያ የምትልክበት ቁልፍ መተላለፊያን መቆጣጠር፣ እና ከምድር በታች የሚገኙ የኒውክሌር ኃይል ማበልጸጊያ ቁሳቁስ ለማውጣት ኮማንዶዎችን ወደ ወደ ቦታው መላክን ያካትታሉ። The post እስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ እንደገና ጥቃትን ለመጀመር እየተዘጋጁ ነው appeared first on Ethiopia Observer .
Original source: Ethiopia Observer